ኢትዮ ስኳር ማኑፋክቸሪግ ኢንዱስትሪ አክስዮን ማኅበር በደቡብ ኦሞ ዞን ሐመር ወረዳ ልዩ ሥሙ ቆርጮ ቀበሌ የስኳር ፋብሪካ ለመገንባት ማቀዱን የኢትዮ ስኳር ፕሮጀክት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቢተው ዓለሙ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል። ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለውም፣ አሁን ላይ በቅድመ ሁኔታ ለሸንኮራ አገዳ መትከያ የሚሆነውን ማሳ በማጽዳትና በማስተካከል የእርሻ ሥራው ተጀምሯል ብለዋል። የስኳር ምርት ሥራ ሰፊ ከመሆኑ አንጻር ወደ ምርት ለመግባት ሦስት ዓመት እንደሚፈጅም ጨምረው ተናግረዋል።

ፋብሪካው በ10 ሺሕ ሄክታር መሬት ላይ እንደሚገነባ የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ አያይዘውም የሚገነባበት ቦታ ለስኳር ምርት ምቹ መሆኑን፣ የአፈር ሁኔታውን፣ የአየር ንብረቱን እንዲሁም ውኃ ገብነቱን በማጥናት ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል።
እንዲሁም ቦታው አስቀድሞ በልማት ባንክ ሥር እንደነበር እና ኢትዮ ስኳር በጨረታ አሸንፎ ከልማት ባንከ እንደገዛው ጠቁመው፣ ለእርሻ ሥራ አስፈላጊ የሆኑ እንደ ትራክተር እና ዶዘር የመሳሰሉ ከ100 በላይ ሜካናይዘድ የእርሻ መሣሪያዎች መኖራቸውን ጠቅሰዋል። 

Contact Us

Ethio Sugar Manufacturing S.C

+251116160001
+251116160002
+251116160003
info@ethiosugar.com

Genete Limate Building office no 755/29-3,
Africa Avenue,Woreda 3, Bole sub city,
Addis Ababa,Ethiopia

Copyright © 2024 Ethio Sugar Manufacturing S.C